Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 14, 2026 .

“የበርበራ ኮሪደርና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ኢንሹራንስ” የፓናል ውይይት ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል።

 

ከሶማሌላንድ የኢንሹራንስ ጉባኤና ኤክስፖ 2026 ጎን ለጎን በተካሄደው “የበርበራ ኮሪደርና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ኢንሹራንስ” የፓናል ውይይት ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል።

በጉባኤው ላይ ከአሜሪካ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከአፍሪካ የተውጣጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከሚገኙት 44 ወደብ አልባ አገራት አንዷ እንደሆነችና ከሁሉም በላይ ባለብዙ ሕዝብ ነገር ግን ወደብ አልባ አገር መሆኗ በኢኮኖሚው ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ በአፅንዖት ተገልፆል።

ኢትዮጵያ በሰላማዊ፣ በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተና ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ ትብብር አስተማማኝና ዘላቂ የባሕር በር ተደራሽነት እንድታገኝ የቀጣናው እንዲሁም የዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም፤ በንግድ ኮሪደሮች ላይ አስተማማኝ፣ ተደራሽና በተገቢው ሁኔታ የተደራጀ የኢንሹራንስ ስርዓት መፍጠር ያለውን አስፈላጊነት በተመለከተ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን:-

ለዚህም ፤ የንግድ ብድር፣ የሞተር ተሽከርካሪ ፣ የየብስ መጓጓዣ ፣ የባሕርና የጭነት ኢንሹራንስን እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ማካተት እንደሚገባ ተገልጿል።

የተቀናጀ የኢንሹራንስ ስነ-ምህዳር መገንባት ከድንበር ተሻጋሪ ንግድ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ ኩባንያዎችን ለመጠበቅ፣ የዕቃዎችን ፍሰት ለማቀላጠፍ እንዲሁም ቀጣናዊ ኢንቨስትመንትና ንግድ ላይ የግሉ ዘርፍ ያለውን እምነት ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።
❇️❇️❇️❇️❇️
Dr. Kenenisa Lemi, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), participated as a panellist in a discussion on “Berbera Corridor and Cross-Border Trade Insurance” held alongside the Somaliland Insurance Summit and Expo 2026.

The summit brought together delegates from the United States, the Middle East and Africa. During the discussion, emphasis was placed on the economic implications of Ethiopia’s landlocked status. Ethiopia is one of the world’s 44 landlocked countries and, notably, one with a large population.

A call was made for regional and international stakeholders to support Ethiopia in securing reliable and sustainable access to the sea through peaceful cooperation based on mutual benefit and win-win partnerships.

The discussion also highlighted the importance of establishing a reliable, accessible and well-organised insurance system along trade corridors.

Such a system should encompass trade credit insurance, motor vehicle insurance, inland transit insurance, marine and cargo insurance, as well as other relevant insurance services.

Developing an integrated insurance ecosystem would play a vital role in reducing risks associated with cross-border trade, protecting businesses, facilitating the movement of goods, and strengthening private-sector confidence in regional investment and trade.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia