Feb 26, 2025 .
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ከኢትዮጵያ ቻምበር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዛሬ አዲስ ከተመረጡት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ፕሬዝደንትና የስራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር ወደፊት በሚኖረን የስራ ግንኙነት ዙሪያ እጅግ ጠቃሚ እና ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል::
በውይይታችን አዲስ የተመረጡት አመራሮች ምክርቤቱ የንግዱን ማህበረሰብ ፍላጎት እና መሻት በሚያሳካ አግባብ ሪፎርም ለማድረግ መወሰናቸውን ገልፀውልኛል:: ውሳኔያቸው የሚያበረታታ በመሆኑ የሚኒስቴር መስሪ ያቤታችን ትብብርና ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልፀንላቸዋል::
የኢፌድሪ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ

