Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

በአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስምምነት ዙሪያ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራ ምክር ቤት ከGIZ-AU ጋር በመተባበር ያሰናዳው የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነት ዙሪያ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ፡፡

በመድረኩ ስለ ስምምነቱ ይዘት፣ በግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴ ላይ በሚኖረው አንደምታ፣ ስምምነቱን ከመተግበር አንፃር በአሁኑ ወቅት በመንግስት በኩል በመከናወን ላይ ስላሉ ተግባራት እና ሌሎች ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የምክር ቤቱ ዋና ጸኃፊ አቶ ውቤ መንግስቱ በግንዛቤ መፍጠሪያው መድረክ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አባል እንደመሆንዋ በእነዚህ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነትዋን ማሳደግ ይኖርባታል፡፡

ለዚህም መሳካት በተለይ የሀገሪቱን የግል ዘርፍ የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮች በየጊዜዉ በመፍታት  ተወዳዳሪነቱን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ይህም የመንግስትና የግል ዘርፉ ዘላቂ ዉይይትና ትብብር ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እነዚህ ተልዕኮዎች ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ አምራቹና የንግዱ ህብረተሰብ በአለም አቀፍና በአገር ደረጃ በሚወጡ ንግድና ኢንቨስትመንትን በሚመለከቱ ህጎች፣ ፖሊሲዎች እንዲሁም ስምምነቶች ዙሪያ በቂ መረጃና ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኮች በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia