የአገር ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያቀጭጨዉን ህገ ወጥ ንግድ ለማስቆም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካለት ተቀናጅተዉና ተናበዉ መስራት እንዳለባቸዉ ተገለፀ።


የአገር ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያቀጭጨዉን ህገ ወጥ ንግድ ለማስቆም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካለት ተቀናጅተዉና ተናበዉ መስራት እንዳለባቸዉ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባካሄደዉ 4ኛዉ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ አገር አቀፍ ጉባኤ ላይ በተደረገ የፓናል ዉይይት ላይ ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል ስራ ዉስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸዉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት በፓናሊስትነት ተካፍለዋል።
ፓናሊስቶቹም በጉሙአሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዝዘዉ ጫኔ፣ በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር የአገር ዉስጥ ንግድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሊቁ በነበሩ፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ የታክስና ጉሙሩክ ወንጀል ምርመራ መምርያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አማን ሆቦሮ እና ከብሔራዊ የመረጃ ደህንነት የህገ ወጥ ንግድና የግብር መረጃ መምርያ ኃላፊ አቶ ቦንያ ለማ ሲሆኑ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ ዉይይቱን መርተዋል።

በተደረገዉ የፓናል ዉይይት ላይም ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል ተቋማቱ በተናጠል የሚያደርጉት ጥረት የሚጠበቀዉን ዉጤት አለማምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ችግሩን ለመግታት የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍና ማህበረሰቡ ተቀናጅቶ መስራት የግድ እንደሚል ተገልጿል።
በጉባኤዉ ላይ የመንግስት አሰፈፃሚ አካላትና የግሉ ዘርፍ በየፊናቸዉ ህገ ወጥ ንግድን ከማስቀረት አንፃር ባሉባቸዉ ክፍተቶችና ማድረግ በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።
በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ህገ ወጥ ንግድን ለማስቆም በአገር አቀፍ ደረጃ ተቀናጅቶ የሚሰራ ብሔራዊ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኮሚቴዉ አስተባባሪ ሲሆን የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ብሔራዊ የመረጃ ደህንት አባል ሆነዉ ተሰይመዋል።




Government and private sector representatives have called for closer cooperation to tackle illegal trade, warning that it continues to weigh on the country’s economic growth.
The appeal came during the 4th National Anti-Illicit Trade Summit organised by the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA).
Participants said isolated efforts had failed to deliver meaningful results and stressed the need for a coordinated national response.
At the end of the meeting, a national committee was set up to strengthen collaboration and intensify the fight against illegal trade.

