Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 27, 2026 .

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬከተሮች ቦርድ ጋር  መክሯል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬከተሮች ቦርድ ጋር በክልሉ ያሉ የንግድ ም/ቤቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሐዋሳ ከተማ ምክክር አካሔደ ።

የምክክሩ ዓለማም የሲዳማ ክልል ምክር ቤቶች ለማጠናከር ከመንግስት ድጋፍ በሚያስፈልግበት ሁኔታ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አስረድተዋል።

የሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ በበኩላቸው የክልል ምክር ቤቶች እንዲጠናከሩ፣ አገር አቀፉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ትኩረት ሰጥቶ ተገቢዉን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ገልፀዉ በክልል ደረጃ እንደ ተቋም እየተደገፉ አለመሆኑን አስረድተዋል። ችግሩ በታችኛዉ የመንግስት መዋቅር ደረጃም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ነጋዴዉ የንግድ ፈቃድ በሚያድስበት ወቅት የአባልነት ፎርም እንዲሞላና የአባልነት መዋጮ ለም/ቤቱ እንዲከፍል ለማስቻል ከንግድና እና ገቢዎች ቢሮ ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት ቢፈረምም የሚፈለገዉን ያህል ውጤታማ መሆን አለመቻሉን አንስተዋል፡፡

የቅንጅት ማነስ እንደ ችግር የተነሳ ሲሆን ሁሉም የመንግስት ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አንድ ሆኖ በመስራት ለአገር ዕድገት አስተዋፅኦ ማበርከት እንዲገባም ገልጸዋል አቶ ዘሪሁን።

የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ያነሷቸዉ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia