Jan 27, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሀዋሳ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እያስገነባው ያለውን የህንፃ ግንባታ ጎበኙ::

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ቢሮ እና ምክር ቤቱ እያስገነባው ያለውና በጅምር ላይ የሚገኘውን የህንፃ ግንባታ ጎበኙ::
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር እንደገለፁትም ሁለቱ ምክር ቤቶች በቅንጅት አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል::



