Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 27, 2026 .

አዲስ ቻምበር ለክፍለ ከተማ የቅርንጫፍ አመራሮች የመሰረታዊ የማህበራት አመራርነትና የፖሊሲ አድቮኬሲ ስልጠና አካሄደ፡ ፡

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት( አዲስ ቻምበር) ለክፍለ ከተማ የቅርንጫፍ አመራሮች የመሰረታዊ የማህበራት አመራርነትና የፖሊሲ አድቮኬሲ ስልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር አካሄደ፡ ፡

አዲስ ቻምበር በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞችና በየወረዳዎቹ በነጋዴው የተመረጡ አመራሮችን እና አስተባባሪዎችን አደራጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፤ ፤

እያንዳንዱ ክ/ከተማ  ከንግድና ዘርፍ የተውጣጡ ሰባት አመራሮች /ወኪሎች አሉት፡ ፤በ11ዱም ክፍለ ከተሞች  ያሉ ከ70 በላይ አመራሮች በዛሬው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ ተሳትፈዋል።

ስልጠናውን እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብሩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ ቻምበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጂ አበበ ጉርሜሳ እንደተናገሩት የየክፍለ ከተሞችና የወረዳ የአዲስ ቻምበር የቅርንጫፍ አመራሮች  የንግዱን ሕ/ሰብ የቅርብ አገልጋዮች እንዲሆኑ አሳስበው ከአመራሮቹ ታማኝነት፤ግልጽነት እና አባላትን ማስቀደም የሚሉት መርሆዎች ወሳኝ መሆናቸውን አብራርተዋል፡:

የአመራር ስልጠናውን የሰጡት የንግድ ም/ቤቱ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ  እንደገለጹት  የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች  በርካታ    የንግዱ  ሕብረተሰብ የሚያነሷቸውን  አስተዳደራዊ ቅሬታዎችን በቅርበት ከሚመለከታቸው ጋር በመመካከር  የሚፈቱበት የአመራር ክሕሎቶች እና የሥነምግባር መርሆዎች ላይ አተኩረው የውይይት መነሻ አቅርበዋል፡፡

በቅርቡ በምክር ቤቱ ቦርድ የፀደቀውና በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ቅርንጫፎች አመራሮች የሚተገበር የውሰጠ ደንብ አሰራር ለአመራሮቹ በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡ ፤

የአዲስ ቻምበር የአደቮኬሲና የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ካሣሁን ማሞ በበኩላቸው በአድቮኬሲ አሰራርና ስልት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ንግድ  ም/ቤቱ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ነጋዴዎች የሚያንሱትን ዋና ዋና የአድቮከሲ ጉዳዮች እና ንግድን ለመስራት ያሉ ከባቢ ሁኔታዎችን በተደራጀ መልኩ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር መፍታት የሚቻልባቸውን ጥበቦች እና ስትራቴጂዎች አመላክተዋል፡ ፤

በእለቱ በተደረገው ወይይት ላይ የየክ/ከተሞች የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት የተደረግ ሲሆን፤  የአቃቂ ቃሊቲ እና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች በአንፃራዊነት የተሻለ  የሥራ አፈጻጸም ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ባለፉት 6 ወራት እንቅስቃሴ ውስጥ የቅንጅት ችግር፤የመረጃ ክፍተት፤ የክትትልና ድጋፍ አናሳ መሆን ፣ የሠው ሀይል እና የክፍለከተማና የወረዳ የቢሮ  እጥረት በተወያዮቹ ከተነሱ ተግዳሮቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡ ፤

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝደንት ወ/ሮ ዘሃራ መሐመድ  ለተነሱት ጥያቄዎችና አሰተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን  በቀጣይ የአዲስ ቻምበር አመራሮችና ሁሉም የሥራ ክፍሎች ለወረዳና ለክ/ከተማ አመራሮች  ትኩረት ሰጥተው  አስፈላጊውን ድጋፍ በማደረግ የተሻለ የሥራ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል፡፡

የአባላት ልማትና ድጋፍ ዋነኛ የምክር ቤቱ ቁልፍ የስትራቴጂ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው ቅርንጫፎችን በሰው ሀይል ፤ በአሰራር እና በመሰረተ ልማት ዙሪያ ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት ውጤት ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ለአመራሮቹ ገልፀዋል።
(አዲስ ቻምበር)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia