Jan 28, 2026 .
የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ ሚናዉን እንዲጫወት ም/ቤቶችን መደገፍና ማጠናከር የግድ መሆኑን የሲዳማ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ አስታዉቀዋል።

የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ ሚናዉን እንዲጫወት ከተፈለገ ንግድ ም/ቤቶችን መደገፍና ማጠናከር የግድ መሆኑን የሲዳማ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ አስታዉቀዋል።
ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና ከክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዲይሬክተሮች ቦርድ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደ ክልል የንግድ ም/ቤት ከእኛ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ነዉ፣ የግሉ ዘርፍና መንግስት ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረዉ አገናኝ የሆነዉ የንግድ ም/ቤት መጠናከር እንዳለበት የክልሉም መንግስት አምኖበት አሰፈላጊዉ ድጋፍ የፖለቲካ ተጠሪዉ በሆነ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እንዲሰጥ አቅጣጫ ተሰጥቶታል ብለዋል።

አገር አቀፉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትም በክልል ደረጃ ያሉትን ም/ቤቶች ለማጠናከር ወርዶ መደገፍ፣መከታተልና ሁሉም ክልሎች ዉክልና እንዲኖራቸዉ የሚያስችል አሰራር መፍጠር አለበት ብለዋል ወ/ሮ ሰላማዊት።

