Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 06, 2025 .

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀውና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በዓለም አቀፍ ገበያ (ኤክስፖርት) ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

   

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀውና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በዓለም አቀፍ ገበያ (ኤክስፖርት) ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በአሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ  ልዩ ትኩረት መሰጠቱና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የማኑፋክቸሪንግ ካውንስል አቋቁሙ በልዩ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምርቶቻቸውን ወደውጭ ሀገራት የሚልኩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በፍጥነት እንዲፈቱና በልዩ ሁኔታ እንዲደገፉ ልማት መ/ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል

ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ሀሳባቸውንና ጥያቄዎቻቸውን በተደራጀ አግባብ ማቅረብ እንዲችሉ፣ ይበልጥ ተሰሚነት እንዲኖራቸውና የሚያጋጥሟቸው ችግሮች እንዲቀረፉ በዘርፍ ማህበራት እንዲደራጁም ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ምርቶቻቸውን ወደውጭ ሀገራት የሚልኩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች፣ ከዘርፍ ማህበራት ም/ቤት፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትና ሌሎች አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት የመጡ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia