የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር አብሮ መስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር አብሮ መስራት በሚያስችሏቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያየ::
በምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የተመራው የማኔጅመንት ቡድን ከሳፋሪክም ኢትዮጵያ የማኔጅመንት አባላት ጋር በተለይም በአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ተግባራዊ ባደረገው የለውጥ ስራ ለንግዱ ማህበረሰብ ከሚጠብቀው አለም አቀፍ ብርቱ ፉክክርና በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ሊኖረው ከሚገባው አበርክቶ አንፃር ሊያዘጋጀው በሚችል መልኩ አቅሙን ለመገንባት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ዶ/ር ቀነኒሳ አስርድተዋል።
አሁን አገራችን የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጫፍ ላይ በደረሰችበት ወቅት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲሁም የብሪክስ አባል በሆነችበት የአገራችን የንግዱ ማህበረሰብ ለሚጠብቀው ብርቱ ፉክክር እራሱን ማዘጋጀት አለበት ያሉት ዋና ፀሐፊው፤ ለዚህ ደግሞ ቢዚነሶች በቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ኢንቨስት ማድረግ ብቻውን ተወዳዳሪ ለመሆን ስለማያስችል ቴክኖሎጂውን ተጠቅሞ ብቁ ተወዳዳሪ ሊያደርጋቸው በሚችል የሰው ኃይልም ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ለዚህ ደግም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የስራ አመራር አካዳሚ ወቅቱን የዋጁ ስልጠናዎችን ስለሚሰጥ በዚህ ዕድል እንዲጠቀሙም አሳስበዋል።


የሳፋሪኮም ኢትዮጵየዓ የውጭ ጉዳዮች ዋና ኃላፊ ዶ/ር አንዱአለም አድማሴ በበኩላቸው ኢትዮጵየዓ ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች ክፍት ባደረገችው የኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ ተወዳድሮ በማሸነፍ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ የሶስት ዓመት ተኩል ዕድሜ ያለው ድርጅታቸው ዛሬ ላይ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት ገልፀው ሳፋሪኮም በስድስት ድርጅቶች የቋቋመ አክሲዮን ማህበር ሲሆን በተለይም የአለም አቀፉ የቮዳፎን ኦፕሬተሮች አባል እነደመሆኑ አገለግሎቱ ፈጣንና ተደራሽ ነው ብለዋል።
መንግስት ምንም እንኳን ምህዳሩን ክፍት ቢያደርግም ዛሬም የግሉ ዘርፍ መሰል አገልግሎት ከሚሰጡት መንግስታዊ ተቋማት ጋር ጀና በአፍሪካ ትልቁ ዩኒየን እንዲሁም አለምአቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን አንስተው፤ አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ በስፔሻሊቲናእንዲወዳደሩ ከማድረግ አኳያ ማመቻቸት እነደሚቀረው ያነሱት ዶ/ር አንዱአለም የግሉ ዘርፍ ድምፅ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከዚህ አንፃር ከፖሊሲ አውጪዎእ ጋር መነጋገር አለበት ብለዋል።
በምክር ቤቱ የአመራር አካዳሚ ከሚሰጡ ስልጠናዎች ጋር በተያያዘ እነደ አገር ከፍተኛ ችግር እንዳለበት በሚታወቀውና የሳፋሪኮምም ችግር ነው ባሉት የማርኬቲንግ ክሎት ላይ ስልጠነው እጅግ እንደሚያስፈልጋቸው የጠቆሙት ኃላፊው የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃርም ከም/ቤቱ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።



