የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ለንግዱ ማኅበረሠብ ” Business and Human rights” በሚል ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ከዳኒሽ ኢንሥቲትዩት ፎር ሂውማን ራይትስ ጋር በመተባበር ለንግዱ ማኅበረሠብ ” Business and Human rights” በሚል ያዘጋጀው ወርክሾፕ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በሚካሄደው ዚህ ወርክሾፕ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፣ ከዳኒሽ ኢንሥቲትዩት ፎር ሂውማን ራይትስ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የንግዱ ማኀበረሠብ ተወካዮች ተሣታፊ ናቸው።
በወርክሾፑ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪል፣ ፖለቲካል እና ሶሺዮ ኢኮኖሚክ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር አብዲ ጅብሪል ኮሚሽኑ በሚሠራቸው የጥናትና ምርምር፣ የአቅም መገንባት እና የምርምር እና ክትትል ሥራዎች ላይ አብርተዋል።
የንግድ ተቋማት ለሠብአዊ መብቶች መጠበቅ ትልቅ አሥተዋጽኦ እንዳላቸው የጠቀሡት ዶክተር አብዲ ነገር ግን ሥህተት የሚሠሩ እንደሚኖሩ በመጠቆም ይህንን ለማሥተካከል በትብብር መሥራት የጠበቃል ብለዋል።
የአሠሪ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀን ሲዎችን፣ የቡና ዘርፍ ላይ ያሉ ሥራዎችን፣ የግንባታ ሥራዎች ላይ ወዘተ ክትትል መደረጉን ጠቅሠዋል ኮሚሽነሩ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሆን ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚቻልም ነው የተናገሩ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ብሥራት በለጠ በበኩላቸው በምክር ቤቱ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ማብራሪያ የሠጡ ሢሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን በማሥወገድ ውጤታማ ሥራ መሥራት የሚያሥችል የለውጥ ተግባራት መተግበራቸውን አንሥተዋል። በሌላ በኩል በንግዱ ማኅበረሠብ ዘንድ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ምክር ቤቱ በትኩረት እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
የዳኒሽ ኢንስቲትዩት ፎር ሂውማን ራይትስ (Danish Institute for Human Rights) የምሥራቅ አፍሪካ ተወካይ ዶክተር ኦጆት ሚሩ ኦጁሉ ኢንሥቲትዩቱ የሚሠራባቸውን የትኩረት መሥኮች ያብራሩ ሢሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የሠብዓዊ መብትና የቢዝነስ ግንኙነት መርሆችና ተሞክሮዎች እንዲሁም በቢዝነስ እንቅሥቃሴዎች ላይ ሥለሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ገለጻ አድርገዋል።


