Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 25, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከእናት ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከእናት ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ሁለቱ አካላት የሴቶችን አቅም በመገንባት፣ በስልጠና፣ በፋይናንስ አቅርቦትእንዲሁም በተለያዩ የንግድ ስራዎች ለተሰማሩ ሴቶች የገበያ እድሎችን በማመቻቸት ረገድ በጋራ ለመስራት ተወያይተዋል፡፡

በምክር ቤቱ እንቅስቃሴ እና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያም ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ አብራርተውላቸዋል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው ሪፎርም የሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞችን ለመደገፍናአቅማቸውን ለመገንባት ለብቻው የስራ ክፍል በማደራጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ቀነኒሳ ጠቁመዋል፡፡

በምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ በኩልም አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለመስጠት እና በሴቶች ላይ የሚስተዋሉ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ከእናት ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት የምክር ቤቱ ፍላጎት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በሚከናወኑየምርትና አገልግሎት ማስተዋወቂያ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሁም ሌሎች የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይቶች ሴቶች የገበያ እድል እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡

የእናት ባንክ የወሜን ባንኪንግ ሶሉሽን (Women Banking Solution) ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ተናኘ ባሳ በበኩላቸው ባንኩ የሴቶችን አቅም በማሳደግ፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ የብድር አገልግሎትን በማመቻቸት እንዲሁም ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የስራ እድል በማመቻቸት ረገድ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍማኅበራት መስራት ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከስልጠና፣ አካታች የፋይናንስ አቅርቦት ባለፈ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ከመንግስት ተቋማት ጋር በመነጋገር የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የውይይት ፕሮግራሞችን(Public-Private Dialogue) ማዘጋጀትና ችግሮቻቸው መፍትሄ እንዲያገኙ ለማስቻልም በጋራ እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia