Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 13, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አፍሪካ ኢን ሞሽን (Africa in Motion) ከተሠኘ ተቋም ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አፍሪካ ኢን ሞሽን (Africa in Motion) ከተሠኘ ተቋም ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።
ሁለቱ ተቋማት በተለይም በአቅም ግንባታ፣ በሥልጠና፣ በወጣቶች፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ዙሪያ እንደሚሠሩ ተጠቁሟል።
የሥምምነት ፊርማውን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር)፣ የአፍሪካ ኢን ሞሽን ዳይሬክተር ማክሥ ኮፊ እና የኢኳል ትሬድ ዎሜን አሊያንሥ (Equal Trade Women Alliance) ኃላፊ ወይዘሮ እንግዳየ እሸቴ ናቸው።

 
የተፈረመውን የሥምምነት ሠነድ ወደ ተግባር በመቀየር በኢትዮጵያ በቴክኖሎጅ የተደገፈ የአቅም ግንባታ፣ አድቮኬሲ፣ በወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም በቢዝነሱ ውስጥ ያሉ አካል ጉዳተኞችን ለመደገፍና በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ልማት ላይ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተነስቷል።
አፍሪካ ኢን ሞሽን በአፍሪካ ማህበረ- ኢኮኖሚያዊ ችግሮን ለመቅረፍና ከአውሮፓ ጋር በማስተሳሰር መፍተሄ ማምጣት ብሎም በኢኳል ትሬድ አሊያንስ በኩል በአካባቢያዊ አቅም ማሳደግ እና በዓለም የንግድ ሂደት ውስጥ የአፍሪካን አበርክቶ ማሳየት ላይ በማትኮር የሚሰራ ነው፡፡
በሥምምነት ስነ ስርዓቱም የአፍሪካ ኢን ሞሽን ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ወልደሠማያትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎች የምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia