Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jun 18, 2025 .

ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ከዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ከዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ የግል ዘርፍ እና በዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት መልካም እድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡
ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ምክር ቤቱ በሚሰራቸው ዋነ ዋና ተግባራት እንዲሁም በግሉ ዘርፍ ላይ ስለሚኖረው አስተዋጽኦ ለኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ገልጸውላቸዋል፡፡
የዓለም ባንክ ግሩፕ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሲንየር ኢኮኖሚስት ጆሴ ሲኞሬት በበኩላቸው በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትና ተጽእኖው ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ በኢትዮጵያም ሊኖረው በሚችለው ተጽእኖ ዙሪያ አብራርተዋል፡፡


ከኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጋር በተያያዘ ሊመጡ የሚችሉ መልካም እድሎችን ለመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ የግሉ ዘርፍ ጉዳዩን በአግባቡ መረዳት እንደሚገባውም ተጠቁሟል፡፡
በውይይቱም የዓለም ባንክ ግሩፕ የንግድና ኢኮኖሚ ፖሊሲ ኢኮኖሚስት ማይክ ንያዎ እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ተገኝተዋል፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia