የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብር በኢትዮጵያ ከኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ አምባሣደር ፋይዘል ቸሪ ሲዳርታ ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብር በኢትዮጵያ ከኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ አምባሣደር ፋይዘል ቸሪ ሲዳርታ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያንና የኢንዶኔዥያን ንግድና ኢንቨሥትመንት ግንኙነት ማሣደግ በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል፡፡
ኢንዶኔዥያ እና ኢትዮጵያ ያላቸው የንግድ ልውውጥና የኢንቨሥትመንት መጠን እያደገ መምጣቱንና በኢትዮጵያም የኢንዶኔዥያ ኩባንያዎች በሥራ ላይ መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አቶ ሰብስብ አባፊራ ምክር ቤቱ በንግድና ኢንቨሥትመንት፣ በአቅም ግንባታ፣ በምርምርና አድቮኬሲ እንዲሁም በሌሎች መሥኮች በሚያከናውናቸው ተግባራትና ከኢንዶኔዥያ ጋር ያለውን የቢዝነስ ትስስር ለማሣድግ በሚችሉባቸው ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ አብራርተውላቸዋል።
በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉ የኢኮኖሚ ለውጦች እና አገሪቷ ለውጭ ባለሀብቶች ባሏት የኢንቨሥትመንት አማራጮች ላይ ማብራርያ የሰጧቸው አቶ ሰብስብ የኢንዶኔዥያ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አምባሳደር ፋይዘል ቸሪ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሀገር እየሆነች መምጣቷንና ኢንዶኔዥያም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ጥቅምት ወር በጃካርታ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያ የቢነዝነስ ተቋማት እንዲሣተፉም አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

