Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 18, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ከተርኪዬ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ላኪዎች ማኅበር ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ከተርኪዬ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ላኪዎች ማኅበር ጋር ተወያዩ፡፡
የማኅበሩ የቦርድ አባላትና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት እና ንግድ ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ አምራች ተቋማት ጋር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
አቶ ጸደቀ ድጋፌ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ፣ በኤሌክትሪክና በኤሌክሮኒክስ ዘርፍ መስራት በሚችሉባቸው እድሎች ዙሪያ አብራርተውላቸዋል፡፡
የማኅበሩ አባላትም በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክና በኤሌክትሮኒክስ በተለይም በኬብል፣ ጀነሬተርና በሌሎችም ዘርፎች ለማምረትና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ የካቲት ወርም በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡና ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት ለማካሄድና በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉ አንስተዋል፡፡
የተርኪዬ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ላኪዎች ማኅበር  አባላትም የፊታችን ጥር 27-የካቲት 1/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 15ኛው ኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
የተርኪዬ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ላኪዎች ማኅበር በኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም በኃይል ዘርፍ የሚሰራ ከ4 ሺ በላይ አባላት ያሉት ማኅበር ነው፡፡


Mr. Tsedeke Digafie, Deputy Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), talks with the Türkiye Electrical and Electronics Exporters Association.
The association’s board members and experts discuss possible investment and trade prospects in Ethiopia, as well as options for cooperating with Ethiopian companies working in the electric and electronic sector.
The delegation members also expressed the need to work together with their Ethiopian counterparts.
Mr. Tsedeke discussed the trade and investment potential open to Türkiye businesses, as well as possibilities for cooperation with Ethiopian companies operating in electric and electronics.
Next February, a delegation from Türkiye Companies will visit Ethiopia for a business meeting with Ethiopian counterparts.
Members of the association are also invited to participate in the 15th Ethio Chamber International Trade Fair, which will be held in Addis Ababa from February 4 to 8, 2026.
The Türkiye Electrical and Electronics Exporters Association works on electrical-electronics and energy and has 4,000 members across the country.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia