Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jun 25, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ቡድን በጃፓን ኦሳካ ከተማ ከጃፓን ኩባንያዎች  ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት አካሄደ::

የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ቡድን በጃፓን ኦሳካ ከተማ ከጃፓን ኩባንያዎች  ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት አካሄደ::
(ኦሳካ ጃፓን – ጁን 26, 2025 ) በኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ምህበራት ምክር ቤት እና በጃፓን የኢትዮጵያ ኤንባሲ በጋራ ትብብር እንዲሁም በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናው ትስስር  ሚኒስቴር ፤ በኢንደስትሪ ፓርኮችና በዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጠንካራ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የጃፓን – ኦሳካ የንግድ ትርኢት አካል የሆነው የአቻ ለአቻ ዉይይት ዛሬ ተካሂዷል:

በውይይቱም፣ ተወካዮቹ በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በኢንዱስትሪ ልማት ዙርያ ሰፊ ዉይይት  ያደረጉ ሲሆን በጋራ ሊተገበሩ በሚችሉ ስራዋች ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሷል ::

በውይይቱም በጃፓን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ፤ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ምህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን ጨምሮ
ሌሎች ኃላፊዎችና ከሁለቱም አገራት የተወጣጡ የንግዱ ማኀበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia