Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 13, 2025 .

የኢትዮ -ደቡብ ኮሪያ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተካሄደ።

የኢትዮ -ደቡብ ኮሪያ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተካሄደ።

በፎረሙም ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሣደር ደዋኖ ከድር፣ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሣደር ካንግ ጁንግ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አይናለም ዓባይነህ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ፣ የኮሪያ ስፔሻሊቲ ተቋራጮች ማኀበር ( Korea Specialty Contractors Association)  ኃላፊዎችና የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

አምባሣደር ደዋኖ ከድር የኮሪያ ስፔሻሊቲ ተቋራጮች ማኀበር በኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ ለመሠማራት ያሣየው ፍላጎት የሚበረታታ ሲሆን በተለይም በጥራታቸው የሚታወቁት የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ወደ ሥራ እንዲገቡ ይበረታታሉ፣ ለዚህ መንግሥትም ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

ዶክተር ዓይናለም አባይነህ በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ትብብር የሀገራቱን ቀጣይነት ያለው ተጠቃሚነት ለማሣደግ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሠው ምክር ቤቱም የውጭ ኩባንያዎችን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም በግሉ ዘርፍና በመንግሥት መካከል አገናኝ ድልድይ በመሆን እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

ሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ታሪካዊና ሁለንተናዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ የኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በሥራ ላይ ስለመሆናቸው በፎረሙ ላይ ተጠቁሟል።

ፎረሙም ወደ የረጅም ጊዜ የኢንቨሥትመንት አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ሲሆን በአይሲቲ፣ በማምረቻ መስኮች፣ በግንባታ፣ በኃይል አቅርቦት እና በመሣሠሉት ዘርፎች መሠማራት እንደሚችሉና ለዚህም ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መኖሩ በፎረሙ ላይ ተጠቁሟል።

የኮሪያ ስፔሻሊቲ ተቋራጮች ማኀበር ( Korea Specialty Contractors Association) ፕሬዚዳንት ሀክ ሱ ዩን ሠፊ ዓለም አቀፍ ልምድ ያለው ማኅበራቸው በኢትዮጵያም በግንባታው ዘርፍ የመሠማራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia