Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 01, 2026 .

የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከትግራይ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከትግራይ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብር እንዲሁም የትግራይ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል አቶ በሪሁ ሀፍቱ ናቸው፡፡

ስምምነቱ በሁለቱ ንግድ ምክር ቤቶች መካከል ጠንካራ የስራ ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር ለማስቻል ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ በተካሄደ ውይይትም ንግድ ድንበር፣ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ቀለም እና ማንነት የለውም ያሉት አቶ ሰብስብ አባፊራ ስምምነቱ የሁለቱን ክልል የንግድ ማኅበረሰብ ለማቀራረብና አብሮ ለመስራት እንዲሁም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል የንግዱ ማኅበረሰብ የሚያጋጥሙ ችግሮች የሁላችንም ችግሮች በመሆናቸው እንዲፈቱ እንደ ኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ ራሱን በማጠናከር መስራት እንደሚገባ ያነሱት አቶ ሰብስብ ስምምነቱና በትብብር መስራቱ በሁለቱ ክልሎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎች ዘንድም እንደ አርዓያ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል አቶ በሪሁ ሐፍቱ በበኩላቸው የሁለቱ ክልሎች የንግድ ምክር ቤቶች በዚህ መልኩ የተፈረመውን ስምምነት ወደ ተግባር በመቀየር የንግዱን ማኅበረሰብ በማቀራረብና በትብብር እንዲሰራ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የሁለቱ ምክር ቤቶች መተባበርና በጋራ መስራት እንደ አንድ ህዝብ ለመስራትና ሀገራዊ የኢኮኖሚ መለውጥ ለማምጣት ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

በስምምነት ስነ ስርዓቱም የሁለቱ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የቦርድ አባላትና የስራ ኃላፊዎቸ ተገኝተዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia