15ኛዉ አለም አቀፍ የኢትዮ ቻምበር ንግድ ትርኢት አገር አቀፍ ዐብይ ኮሚቴ ሁነቱን ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር መክሯል።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትብብር ከጥር 27 እስከ የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደዉ 15ኛዉ አለም አቀፍ የኢትዮ ቻምበር ንግድ ትርኢት አገር አቀፍ ዐብይ ኮሚቴ ሁነቱን ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር መክሯል።
የአገር አቀፍ ዐብይ ኮማቴዉ ሰብሳቢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር አብዱልሀኪም ሙሉ ኮሚቴዉ የተዋቀረዉ ይህንን የአገሪቱን ንግድና ኢንቨስትመን በማስስፋፋትና ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በማስተዋወቅ ኢንበስትመንትን በመሳብ ዉስጥ ጉልህ ሚና ካላቸዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተዉጣጡ የስራ ኃላፊዎች መሆኑን ጠቅሰዉ ሁሉም ለማሳካት የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በቀሪዉ ጊዜ ዉስጥ ስራዉን ለማሳካት የድርጊት መርሐ ግብር አዉጥቶ በተቀናጀ ሁኔታ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም በአፅንኦት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ እስከ አሁን ድረስ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለኮሚቴዉ አቅርበዋል።
አገር አቀፍ የ15ኛዉ አለም አቀፍ የኢትዮ ቻምበር ንግድ ትርኢት ዐብይ ኮሚቴ አባላት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ከግብርና ሚኒስቴር፣ከማዕድን ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተዉጣጡ ናቸዉ።

