Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 15, 2025 .

የኦንላይን የጉምሩክ አገልግሎት ምንነት ዙሪያ ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነውን መረጃ እናጋራችሁ

ውድ የቻናላችን ተከታዮች  ለዛሬ
የኦንላይን የጉምሩክ አገልግሎት ምንነት ዙሪያ ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነውን መረጃ እናጋራችሁ
❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
✍️ ኦንላይን የጉምሩክ አገልግሎት ማለት የጉምሩክ ደንበኞች ወደ ጉምሩክ ኮሚሽን በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው፡-
• በኢንተርኔት አማካኝነት ኦንላይን ዲክላሪስዮን የመሙላት፣
•  መረጃዎችን የመላክ እና የመቀበል፤
•  እንዲሁም የጉምሩክ አፈጻጸሙ የሚገኝበትን የጉምሩክ ሂደት መከታተል የሚችሉበት የድህረ-ገጽ ኔትወርክን በመጠቀም የሚፈጸም የጉምሩክ አገልግሎት ነው፡፡

✍️ አገልግሎቱ ዲክለራሲዮን ለመሙላትና ለጉምሩክ ለመላክ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ዕቃ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትም ሆነ ከሀገር ለማስወጣት ለሚፈልግ ግለሰብ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን ማግኘት የሚችልበትን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህንን አገልግሎትም የይለፍ ቃል እና ፓስወርድ ሳያስፈልገው መጠቀም የሚቻልበት ሲሆን  ለአብነትም ሊከፈል የሚገባውን የቀረጥና ታክስ መጠን ለማወቅ ተጠቃሚው፡-

https://customs.erca.gov.et/trade/ የሚለውን አድራሻ ዌብ ብሮውዘር ላይ በማስገባት  በጉምሩክ  ሲስተም  (TPM)  የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን ‹‹SEARCH TARRIF›› የሚለውን በመጠቀም ‹‹TAX SUMULATOR›› የሚለውን በመጫን እና የሚጠየቁ አስፈላጊ መረጃዎችን ብቻ በማስገባት ‹‹Calculate›› የሚለውን ቁልፍ በመጫን ሊከፈል የሚገባውን የቀረጥና ታክስ መጠን ማወቅ ይችላል፡፡

• የታሪፍ ኮድ (HS code) መግለጫ (Tarrif Description) እና
• የታሪፍ ምጣኔ (Tariff Rate) ማግኘት ይቻላል፤

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia