በቡና ኤክስፖርት ብቻ በበጀት አመቱ ሶስት ወራት ከ762.75 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተገኝቷል ፡- ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን

በቡና ኤክስፖርት ብቻ በበጀት አመቱ ሶስት ወራት ከ762.75 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተገኝቷል ፡፡
በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት 151,969.41 ቶን ቡና በመላክ 622.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 113,542 ቶን (ከዕቅዱ 75%) በመላክ 762.75 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 123%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ 243.73 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር (47%) ገቢ ጭማሪ የተመዘገበበት ነበር፡፡
በ2018 በጀት ዓመት ሶስት ወራት የተላከዉ ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ
ጀርመን በመጠን 20,793.14 ቶን (18%) እና በገቢ 138.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (18%) ድርሻ፣
ሳዉድ አረቢያ በመጠን 16,088.45 ቶን (14%) እና በገቢ ደግሞ 102.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (13%) ድርሻ እንዲሁም
ቤልጅዬም በመጠን 13,910.92 ቶን (12%) እና በገቢ 93.45 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (12%) አፈፃፀም በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፤
የቀሩ መዳረሻዎች በ2018 ገቢ ቅደም ተከተል 4ኛ ቻይና፣ 5ኛ አሜሪካ፣ 6ኛ ደ.ኮሪያ፣ 7ኛ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ 8ኛ ጃፓን፣ 9ኛ ጣልያን እና 10ኛ ራሽያ ፈደሬሽን መሆናቸውን እና ከ1 እስከ 10 ያሉት በአጠቃላይ በመጠን 80% እና በገቢ 79% የዉጪ ምንዛሪ ግኝት መሸፈን መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
በጥቅሉ የእነዚህ ዋና 10 መዳረሻ ሀገራት ከ2017 አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር በመጠን 3% እና በገቢ ስታይ የ52% ጭማሪ አላቸው፡፡
በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ በጀት አመት ኤክስፖርቱን ለማሳደግ ከተከናወኑ እጅግ በርካታ ተግባራት መካከል፤
እንደ ቻይና ባሉ አዳዲስ መዳረሻ ሀገራት ላይ የገበያ ማስፋፊያ ስራዎች መሰራታቸው፤
የመረጃ ጥራትን ከማሳደግ እና የቡና ግብይት ቁጥጥርን ዘመናዊ ከማድረግ አንጻር የቡና መረጃ ዳታቤዝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ለመዘርጋት በታቀደው መሰረት ከሽኝት ጣቢዎች በየዕለቱ የሚሸኝ ቡና በሲስተም እንዲደገፍ መደረጉ፡፡
በየወሩ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ የገበያ መረጃዎችን በማደረጃት እና በመተንተን ለግብይት ተዋንያንና ለባለድርሻ አካላት እንዲደርስ በማድረግ በኮንትራት አገባብ የአፈጻፀም ሂደቱን እንዲቀላጠፍ መደረጉ፣
ቡና ላኪዎች ያላቸውን ክምችትና የገቡትን ኮንትራት መሠረት በማድረግ ቡናን በወቅቱ ወደ ውጭ በመላክ ከዘርፉ የሚጠበቀውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ግኝት ለማስገኘት የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል መደረጉ፤
ባለስልጣኑ የሚያወጣው ሳምንታዊ የቡና ዝቅተኛ ኮንትራት መሸጫ ዋጋ ከዓለም ዓቀፍ የቡና ዋጋን በመተንተን በወሩ በታቀደው መሠረት እንዲሰራጭ መደረጉ፤
ከተለያዩ አገራት ጋር በተለይም የተሻለ የቡና አመራረት ልምድ ካላቸው አገራት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከርና የኢትዮጵያን የቡና ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ማካሄድ መቻሉ ተጠቃሽ መሆናቸውን ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ጨምረው አስረድተዋል፡፡(ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን)

