Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 26, 2026 .

“የድል ሠራዊት!” በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው 119ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

“የድል ሠራዊት!” በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው 119ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

ለሀገራችን አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲሁም ለሕዝባችን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ በትጋትና በቁርጠኝነት ለሚያገለግሉ የመከላከያ ሠራዊታችን አባላት ያለኝን ከፍተኛ አክብሮትና ምስጋና እገልጻለሁ።

ለ119 ዓመታት የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ደኅንነት በመጠበቅ የቆየው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገራችን ጋሻና መከታ ከመሆኑም በላይ ለሀገራዊ መረጋጋትና ለልማት መሠረት የሆኑ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው።

በመከላከያ ሰራዊታችን  የተረጋገጠው የሀገር ሰላምና ደኅንነት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለግሉ ዘርፍ መስፋፋት፣ ለንግድ እንቅስቃሴና ለአገር ውስጥም ሆነ የውጪ ኢንቨስትመንት መስፋፋት ወሳኝ መሰረት ነው።

የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢ መኖሩ ንግዶች በእምነት እንዲንቀሳቀሱ፣ ባለሀብቶች አዳዲስ  የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲፈጥሩ፣ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉና ዜጎች በምርታማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታን ይፈጥራል።

በመጨረሻም ፤ በዚህ ታሪካዊ በዓል የመከላከያ ሠራዊታችን አባላት ለሀገራቸው ለሚያደርጉት አገልግሎትና መሥዋዕትነት
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በራሴ ስም ደጋግሜ አክብሮቴን እየገለፅኩኝ ፤  በዚህ አጋጣሚም ለዘላቂ ሰላምና ለሀገራዊ ብልጽግና መሳካት የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ሁሉ ለመወጣት ያለንን ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia