Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 18, 2025 .

14ኛዉ የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት የመዝጊያ እና የእውቅና መርሀ ግብር

   

የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 14ኛዉ የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት የመዝጊያ እና የእውቅና መርሀ ግብር  እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ ።
በመርሀ ግብሩ ላይም ለአገር ውስጥና ለውጪ ተሳታፊዋች እውቅና የተሠጠ ሲሆን  የንግድ ትርዒቱ  የተሳካ እንዲሆን  ድጋፍ ላደረጉ በተጨማሪም  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተሳታፊዋች ሽልማት ተሰጥቷል ።

 
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ እንደገለፁት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሪነት ሚና የሚጫወት፣ ጠንካራና ዘላቂ አቅም ያለዉ አቅም እንዲፈጠር  ብሎም ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
የግሉ ዘርፍ የአገራችን ኢኮኖሚ ሞተር መሆኑ በተደጋጋሚ መገለጹም በአጠቃላይ ለምንፈልገው አገራዊ ዕድገት  የንግዱ ኅብረተሰብ ተሳትፎ ቁልፍ መሆኑን ለማሳየትም ጭምር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸዉ የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 14ኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ፤ የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ግብዓቶች በማስተዋወቅ፣ ለአገራችን ኢንዱስትሪ ልማት እድገት፣ ለስራ ፈጠራ እና ለንግድ ስራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት እንዲሁም የሀገር ዉስጥና የዉጭ ኩባንያዎች መካከል የገበያ ትስስር፣የእዉቀትና የልምድ ልዉዉጥ የተደረገበት ከመሆኑ አንጻር  ውጤታማ ነበር፡፡
ከዚህም ባሻገር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ይህ ኤግዚቢሽን  ከውጭ የመጡ የንግድ አካላት የተሳተፉበት እንደመሆኑ  ልምድ ለመለዋወጥ እና ትስስር ለመፍጠርም ትልቅ ጠቀሜታ እንደነበረው ገልፀዋል ።


በተያያዘም የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድሎችን የዳሰሰ የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የንግዱ ማኀበረሰብ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተወከሉ የስራ ኃላፊዋች ተገኝተዋል።

   

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia