Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 18, 2025 .

14ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ ::.

የንግድትርዒቱን የከፈቱት የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ

ንግድ ትርዒቱ የሀገር ውስጥ ምርትና አገልግሎቶች የሚተዋወቁበትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ልምድ የሚለዋወጡበት እንደሚሆን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተከፈተው የንግድ ትርዒት ፕሮግራም ላይም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሣደሮች፣ የሀገር ውሥጥ እና የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት  ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚው መሪ እንዲሆን ለማድረግ ምርትና አገልግሎቶች እንዲተዋወቁና ገበያ እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የሀገር ውሥጥ ምርትና አገልግሎቶች  እንዲተዋወቁ እና ንግድና ኢንቨሥትመንት እንዲሥፋፋ የተዘጋጀው 14ኛው ኢትዮ ቻምበር የንግድ ትርዒት ለኩባንያዎች ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።

     
በንግድ ትርዒቱ ግዙፍ የማምረቻ ኢንዱሥትሪዎችን ጨምሮ በርካታ ምርትና አገልግሎቶች ለእይታና ሽያጭ ቀርበዋል።

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia