Jun 11, 2025 .
ለተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫ ቦርድ መልማይ ኮሚቴ ሪፖርት

ከምርጫ ቦርድ መልማይ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አባላት ጋር በመሆን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በተገኙበት ለተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የመልማይ ኮሚቴ ሪፖርት መቅረቡን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቀራርቦ በመስራት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከመገንባት ባለፈ የጋራ በሚያደርጉዋቸው ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያደርጉት ዉይይት የሚደነቅ መሆኑና የመልማይ ኮሚቴ አባላትም ይህ አይነቱ አሰራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በርቱ እንላለን ብለዋል።



