Nov 18, 2025 .
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ደንብ ቁጥር 185/2017 አውጥቷል

የአዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ለውጥ አንፃር የአብዛኛው ማህበረሰብ የሥራ ባህል እና ፍላጎት በመለወጡ የንግድ ሥራዎችንና አገልግሎቶችን በምሽት መከወን እየተለመደ የመጣውን ተግባር ወጥነትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
በከተማዋ በስፋት እየተከናወነ የሚገኘው መሠረተ- ልማት በኢኮኖሚው ላይ የፈጠረውን መነቃቃት አጠናክሮ ለማስቀጥል፣
የሥራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
የንግድና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋማት በምሽት ተግባራቸውን ማከናወን የሚችሉበትን የአሰራር ሥርዓት በህግ መደንገግ በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ደንብ ቁጥር 185/2017 አውጥቷል፡፡ (ተያይዟል)
Read the full pdf file

