Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢትዮ-ቻይና የቢዝነስ ፎረም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሔደ፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያስተዋወቅ የኢትዮ-ቻይና የቢዝነስ ፎረም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሔደ፡፡

በዚህ ከ90 በላይ ከተለያዩ ሴክተሮች የተውጣጡ የቻይና የንግድ ልዑካን በተሳተፉበት ፎረም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንትን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች  እንዲሁም የኢትዮጵያን የንግድ ማኅበረሰብ ተገኝተዋል፡፡

ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ምስጋኑ አርጋ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ቻይና ያላቸው የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ትስስር ረዥም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑንና  ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ  እንደመሆንዋ፤ ከዚህ በፊት የነበሩትን ግንኙነቶች የበለጠ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነት ላይ መስራት  ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም ኢትዮጵያ ባላት ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች የቻይና ባለሃብቶች  ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፎረሙ ላይ   ንግግር ያደረጉት  የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር  ዓይናለም አባይነህ በበኩላቸው  ኢትዮጵያና ቻይና የቆየ ወዳጅነት ያላቸው በተለይም በንግድ ልውውጥ እና ኢንቨስትመንት የጋራ ተጠቃሚነት  መርህን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን የሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ፎረሙ የቻይና የንግድ ልዑካን  ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር በትብብር ለመስራትና አብሮ ለማደግ እድል  የሚሰጥ ከመሆኑ አንፃር የቻይና የንግድ ልዑክ  ከኢትዮጵያ አቻው ጋር    ውይይት ማድረጉ የሁለቱን ሀገራት የጠነከረ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግም ያግዛል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የግሉን ዘርፍ በመደገፍ በተለይም ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና የግሉ ዘርፍ የመሪነቱን ሚና እንዲ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia