Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

በአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነት እና በካፒታል ገበያ ዙሪያ ውይይት

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት የተሠናዳው በአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነት እንዲሁም በካፒታል ገበያ ዙሪያ በተሰናዳው የግንዛቤ መፍጠሪያና የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ ለምክር ቤቱ የዴሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ማኔጅመንት እየተሰጠ ያለውን ሥልጠናው በንግግር የከፈቱት  የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብሰብ አባፊራ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ ከግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎን የሚያበረታቱ ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፤ ደንቦች እና አሰራሮች ከግሉ ዘርፍ ፍላጎት ፣ መብትና ጥቅም ጋር የማይጋጩ መሆን አለመሆናቸውን በመተንተን፣ ጥናታዊ ዘገባዎችን በማዘጋጀትና የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ አሰራሮች፣ፖሊሲዎች፤ ህጎች በሚቀየሩበት አልያም ሊሻሻሉ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ከዚህ አንጻር በነገው ዕለት ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ጋር በትብብር የምናካሂደው 4ኛው የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም  በወጡ ዓለም አቀፍም ሆነ አገራዊ ፖሊሲዎች እና ተያያዥ  ጉዳዮች ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ለሚያንቀሳቅሱ መሪዎች፤ የቦርድ አመራር  እንዲሁም ለንግድ ማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ያመቻቻል።

የዛሬው የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነት እንዲሁም  በካፒታል ገበያ ዙሪያ ለምክር ቤታችን  ለዴሬክተሮች ቦርድ አባላት እንዲሁም ለማኔጅመንቱ የተዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያና የውይይት መድረክ  መነሻም እነዚህ አበይት ዓላማዎቹ ናቸው፡፡ አቶ ስብስብ አክለውም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አባል እንደመሆንዋ በእነዚህ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነትዋን ማሳደግ ይኖርባታል፡፡

ለዚህም መሳካት በተለይ የሀገሪቱን የግል ዘርፍ የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮች በየጊዜዉ በመፍታት ዐቅሙንና ተወዳዳሪነቱን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ይህም የመንግስትና የግል ዘርፉ ዘላቂ ዉይይትና ትብብር ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው የካፒታል ገበያ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች የኢኮኖሚውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያነቃቁና የዕድገት ሂደትን  ከሚቀይሩ የአሰራር ስረሃቶች ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ግልጽና ፍትሃዊ የካፒታል ገበያ የአንድን ሀገር የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስፋት አስተማማኝ የገንዘብ አቅም እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ የግሉ ዘርፍ በትላልቅ የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ የሚኖረውን ተሳትፎ የሚያሳድግ በመሆኑ የተወዳዳሪነት ምህዳሩን በማስፋትና ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ዶክተር ቀነኒሳ አክለውም ፥  የግሉ ዘርፍ በጉዳዩ ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት  በሚጠበቀው ልክ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል፤ለዚህ ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ስልጠናዎች እና የአቅም ማሳደጊያ መድረኮች የሚያስፈልጉ ሲሆን የዛሬው የግንዛቤ ማስጨበጫም የዚህ አንድ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

በሌላም በኩል የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መመስረቻ ስምምነትን እስካሁኑ  ከ55ቱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት 54ቱ የፈረሙት ሲሆን፤ ከፈረሙትም 47ቱ ስምምነቱን ስላፀደቁት የንግድ ቀጣናዉ አባል ሆነዋል፡፡ ከአባል ሀገራቱ መካከልም ሀገራችን ኢትዮጵያ ትገኝበታለች፡፡ የአባላቱ ቁጥርም ከዚህ በላይ ጨምሮ ሁሉንም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የሚያካትት እንዲሆን ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዓላማዎች ለማሳካት በአባል ሀገራቱ የተለያዩ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸዉ ይገልፃል፤ ስራዎቹ እንዲሰሩ የሚያስፈልጉትን የህግና ተቋሟዊ ማዕቀፎችንም ዘርግቷል፡ ፡

ከነዚህም ስራዎች ውስጥ በአባል ሀገራቱ መካከል በሚደረጉ ድርድሮችና ስምምነቶች ቀረጦችንና ሌሎች ቀረጥ ያልሆኑ ለእቃዎች ንግድ ማነቆ የሆኑትን መሰናክሎች ደረጃ በደረጃ ማስወገድና የአገልግሎቶች ንግድ ደረጃ በደረጃ ነፃ ማድረግን ይገኙበታል፡፡

በኢንቨስትመንት፣ አእምሮአዊ ንብረት መብቶች፣ በውድድር ፖሊሲና በሁሉም ንግድ-ነክ ጉዳዮች ላይ መተባበርም ሌላኛዉ ስራ ነዉ፡፡ በተጨማሪ በጉምሩክ ጉዳዮችና በንግድ ማሳለጫ እርምጃዎች ላይ መተባበር፤መብቶቻቸውንና ግዴታዎቻቸውን በሚመለከት የአለመግባባቶችን መፍቻ መንገድ ማቋቋም፣  ቀጣናዉን ተግባራዊ ለማድረግና ለማስፈፀም ተቋማዊ ማእቀፍ መመስረትና ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ሌሎች ሀገራቱ ለመስራት የተስማሙባቸዉ ጉዳዮች ናቸዉ።

ሀገራችን ኢትዮጵያም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አባል እንደመሆንዋ በእነዚህ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነትዋን ማሳደግ ይኖርባታል፡፡ ለዚህም መሳካት በተለይ የሀገሪቱን የግል ዘርፍ የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮች በየጊዜዉ በመፍታት ዐቅሙንና ተወዳዳሪነቱን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ይህም የመንግስትና የግል ዘርፍን ዘላቂ ዉይይትና ትብብር ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እነዚህ ተልዕኮዎችን ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ አምራቹና የንግዱ ህብረተሰብ በአለም አቀፍና በአገር ደረጃ በሚወጡ ንግድና ኢንቨስትመንትን በሚመለከቱ ህጎች፣ ፖሊሲዎች እንዲሁም ስምምነቶች ዙሪያ በቂ መረጃና ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኮች በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia