Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ ከኪሊማንጃሮ ግሎባል አማካሪ እና የስልጠናና ኢኖቬሽን ተቋም ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ ከኪሊማንጃሮ ግሎባል አማካሪ እና የስልጠናና ኢኖቬሽን ተቋም ጋር በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ሁለቱ ወገኖች በሰምምነቱ ትግበራ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በአፍሪካ ገበያ ተጠቃሚ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡

በአማካሪ ተቋሙ በኩል የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ዙሪያ መምሪያ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን ለዚህ ይረዳው ዘንድም ከሚመለከታቸው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑን የተናገሩት የኪሊማንጃሮ ግሎባል አማካሪ፣ የስልጠና እና ኢኖቬሽን ተቋም ማኔጂንግ ዳይክተር ዶክተር አዲስ ካሳሁን ናቸው፡፡

በአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በተመለከተ በምክር ቤቱ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ በሌላ በኩል ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ በወጣቶች እንዲሁም በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማሳደግ እንዲሁም በአፍሪካ ገበያ ተጠቃሚነት ዙሪያ በምክር ቤቱ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ አንስተዋል፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ በበኩላቸው የምክር ቤቱን የሪፎርም ስራዎችና በቅርቡ እየተተገበሩ ባሉ አዳዲስ አሰራሮች እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን አብራርተዋል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ በአፍሪካ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆን የአቅም ግንባታ እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና ወጣቶችን ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ በምክር ቤቱ በኩል እመርታዊ ለውጥ እና ውጤት ለማምጣት እየተሰራ መሆኑንና ነጋዴው በነጻነት እንዲሰራና ተደማጭነት እንዲኖረው ለማድረግም ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው ያሉት አቶ ሰብስብ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እና የኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቶች ገበያ እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ጋርም በቅርበት እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia