Feb 26, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ከአባይ ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ከአባይ ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ አካላት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡
ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ የአድቮኬሲ እና ምርምር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስራዎች ዋነኛ የትኩረት መስኮች መሆናቸውን አንስተው ከባንኮች ጋርም በቅርበት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአባይ ባንክ ተወካዮች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት የፋይናንስ ዘርፉ በለውጥ ሂደት ላይ በመሆኑ እንደ ምክር ቤቱ ካሉ ሀገራዊ ተቋማት ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት የአቅም ግንባታ እና ስልጠናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

