በታክስ ኦዲት ፣ ቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ዙሪያ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡


በታክስ ኦዲት ፣ ቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ዙሪያ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
(የኢንዘማም፡ መጋቢት 24/2017)
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከጂ አይ ዜድ ቤክ (GIZ BEIC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት “Tax Audit and Compliant Handling Practice in Ethiopia” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ ተገኙት የምክር ቤቱ የኢንፎርሜሽንና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ዋቅጂራ ለንግዱ ማኅበረሰብ ምቹ የንግድ ከባቢ ለመፍጠር በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል አገናኝ ድልድይ የሆነው ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጣቸው በማድረግ በኩል ምክር ቤቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በታክስ ኦዲት ላይ እየተሰራ ያለው የጥናት ስራም ምክር ቤቱ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የጂ አይ ዜድ ቤክ ፕሮጀክት ቡድን መሪ ሚስተር አልቤርቶ ጎሜዝ በበኩላቸው መሰል በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ እንደ electronic public- private dialogue ያሉ አሰራሮችን በመዘርጋት እየሰሩ መሆኑን አንስተው የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ላይ ለሚሰሩ የምርምርና አድቮኬሲ ስራዎች አስላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ዘንድ ለጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡


