Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 12, 2025 .

ለኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ማኔጅመንት እና ሠራተኞች “የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶችን ወደ ስኬት መምራት” በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሠጠ።


ስ ልጠናውን የሠጡት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር) ሲሆኑ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችን ውጤታማ ለማድረግ የለውጥ (Reform) ሥራዎች እየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል።
እነዚህን የሪፎርም ተግባራት ሥኬታማ ለማድረግ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማሣያነት ያነሡት ዋና ጸሐፊው በተለይም በሠው ሐብት አሥተዳደር፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ በቅንነትና ታማኝነት እንዲሁም በትልቁ አቅዶ መሥራትና መተባበር ተገቢ ሥለመሆኑ አንሥተዋል፣
በተለያዩ የአመራር ሞዴሎች ዙሪያ ማብራሪያ የሠጡት ዶክተር ቀነኒሳ ምክር ቤቶች ውጤት ተኮር ተግባራትን ያከናውኑ ዘንድ የሥኬታማ አመራር መርሆችን መከተል እንደሚገባቸው አንሥተዋል።
ምክር ቤቱ የሚተገብራቸው የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መሠረታዊ የቻምበር መርሆችንና አሠራሮችን በአግባቡ መተግበር ያሥፈልጋል ብለዋል።


የምክር ቤቶችን የአሠራር ሂደቶችን በመከተል፣ እርስ በርስ በመደጋገፍ፣ የሠለጠነና በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን በማከናወን ሠራተኞች ኃላፊነታችውን መወጣት እንዳለባቸውም ተነሥቷል።
ምክር ቤቱ ለግሉ ዘርፍ ተሠሚነት ያለው ድምጽ እንዲሆን ከምንጊዜውም በበለጠ ከአባላት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፣ በምርምርና አድቮኬሲ ፣ በሥልጠናና በሌሎችም መሥኮች ከመንግሥትና ከልማት አጋሮች ጋር የሚሠሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም ተነሥቷል።
ከሀገር ውሥጥ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በአግባቡ በመረዳት በንግድና ኢንቨሥትመንት ፕሮሞሽን ዙሪያ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣትም የተጠናከሩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተጠቁሟል።
መሠል ሥልጠናዎች የማኔጅመንት እና የሠራተኛውን ግንኙነት በማጠናከር ውጤታማ ሥራ ለመሥራት እንደሚያግዙ ሠልጣኞቹ ገልጸዋል።

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia