Apr 17, 2025 .
የቀድሞው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፡፡
አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ከሚያዝያ/2006 እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም አርፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስም በአቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ህልፈተ ሕይዎት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩኝ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እመኛለው፡፡
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

