Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 23, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር መድረኩ በሁለቱም አገራት ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እድልን ያጎለብታል ሲሉ ተናግረዋል።

 

የኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ ንግድ ም/ቤት የመጀመሪያ ስብሰባ እና የቢዝነስ ፎረም ሚያዚያ 14 ቀን 2017 በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሄዷል።
በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር  መድረኩ በሁለቱም አገራት ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እድልን ያጎለብታል ሲሉ ተናግረዋል።
በሳኡዲ ወገን በኩል በ2030 የሳዑዲ አረቢያ ሁለንተናዊ እድገት ራዕይ የአፍሪካን አህጉር በኢኮኖሚው ዘርፍ ዋና መዳረሻ ያደረገ እንደሆነና ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋር በማድረግ   ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ አብራርተዋል።


ውይይቱ  በሁለቱ አገሮች መካካል ያሉ የንግድ፥ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እድሎችን እየለየና የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈታ በመስኮቹ የሚኖሩ ትብብሮችን  እንደሚያጎለብት የተገለፀ ሲሆን፥ የቢዝነስ ፎረሙ የቀረቡ ሃሳቦችና የንግድ ማህበረሰብ መካከል የተደረጉ ውይይቶች  እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል።  ፎረሙ በግንቦት 2016 ዓ.ም በሁለቱ አገሮች ንግድ ምክር ቤቶች መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የተካሄደ ሲሆን፥ በቀጣይ አመት አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia