Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 15, 2025 .

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ጋር በመተባበር የቢዝነስ ሴሚናር አካሄደ።

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA)  ጋር በመተባበር የቢዝነስ ሴሚናር አካሄደ።
ሴሚናሩ ያተኮረዉ የአገር ዉስጥ አቅራቢ ድርጅቶች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የግዥ ህጎች ላይ ተገቢዉ ግንዛቤ ኖሯቸዉ  UNECA በሚያወጣቸዉ የተለያዩ ጨረታዎች ላይ ብቁ ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ ማስቻል ላይ  ነዉ።
በሴሚናሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ የግሉ ዘርፍ ድምፅ የሆነዉ የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት የግሉ ዘርፍ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲኖረዉ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ በተለይም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዉስጥ ተገቢዉን ቦታ እንዲይዝና ተገቢዉን ሚና እንዲጫወት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እየሰራን ነዉ ብለዋል።


ይህ የዛሬዉ የቢዝነስ ሴሚናርም የግሉን ዘርፍ የተወዳዳሪነት አቅምን ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ  ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) በበኩላቸዊዉ በምክር ቤቱ አጠቃላይ ታሪካዊ ዳራ ራዕይና ተልዕኮ እንዳሁም አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና እያስመዘገበ ባለዉ አበረታች ዉጤቶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia