በሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት በሚካሄደው 13ኛው የኦሮሚያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።




በሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት በሚካሄደው 13ኛው የኦሮሚያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
መድረኩ በሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ግንቦት 23/2017 በሱሉልታ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚካሄድ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው ውይይቱ የተካሄደው።
በውይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ፣ የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ፣ የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት አቶ መገርሣ ረጋሣን ጨምሮ የክልሎች የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አመራሮችና ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የተውጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል።



አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የምክክር መድረኩን አሥመልክተው በዋዜማው በተካሄደ ውይይት ላይ ባሥተላለፉት መልእክት የጠንካራ ምክር ቤቶች ተሞክሮ ወደ ሌሎች ምክር ቤቶች እንዲሥፋፋ እና እንዲጠናከር በሚል የልምድ ልውውጥ መድረኩ መጀመሩን ጠቁመው ላለፉት ዓመታት መቀጠሉንና ዘንድሮም ለ13ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
ምክር ቤቶች ብቁ ሥልጠና መሥጠት እንዲችሉ፣ አድቮኬሲ ላይ እንዲሠሩ፣ የአባላትን አቅም እንዲያሣድጉ፣ ጥንካሬ እንዲስፋፋ ለማድረግ የልምድ ልውውጡ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸል።
መድረኩ ከኦሮሚያ ባለፈ ለሁሉም ክልሎች ልምድ እንዲለዋወጡ እድል የፈጠረ መሆኑን በመጠቆም ንግድ ሀይማኖት፣ ዘርና ድንበር የሌለው በመሆኑ ለሁሉም የንግዱ ማኀበረዝሰብ ትልቅ ሚና ያለው ነው።
የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በአዋጅ የተሠጡትን ተልእኮዎች ግብ ለማድረስ የግሉ ዘርፍ በ2 የሥትራቴጂክ ዘመናት ጠንካራ እና ኢኮኖሚውን የሚመራ እንዲሆን እየሠራ ነው ብለዋል።
ምክር ቤቶች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ እና ውጤታማ ሥራ እንዲሠሩ ለማድረግ በየዓመቱ የልምድ ልውውጥ መድረኩ እየተዘጋጀ መቀጠሉን በዋዜማው በተዘጋጀ ውይይት ላይ የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት መጋቢ ሥርዓት ቀሲስ ታየ ለታ ገልጸዋል።
13ኛው የልምድ ልውውጥ መድረክም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች አመራሮችና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት ነው የሚካሄደው።

