Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 31, 2025 .

በ13ኛው የኦሮሚያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ላይ ሽልማት ተበረከተ።

በሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት በሚካሄደው 13ኛው የኦሮሚያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ላይ ሽልማት ተበረከተ።

ከልምድ ልውውጥ መድረኩ ቀድም ብሎ በተካሄደው ውይይት ለንግዱ ማኀበረሰብ አቅም ግንባታና ለግሉ ዘርፍ መሻሻል እየሠሩ ላሉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ጨምሮ ለሌሎች ክልሎች የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱን ያበረከቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ናቸው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትን ጨምሮ የሌሎች ክልሎች የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ምክር ቤቶች በጋራ እና በትብብር መንፈስ ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ማደግ መሥራት እንዳለባቸው አቶ ሰብስብ አባፊራ መልእክት አሥተላልፈዋል።

በሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት የሚካሄደው 13ኛው የልምድ ልውውጥ መድረክ በዛሬው እለት ግንቦት 23/2017 በሱሉልታ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ይካሄዳል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia