Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jun 10, 2025 .

አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በምክር ቤቱ እና በአባል ምክር ቤቶች መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲኖር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተነስተዋል፡፡


አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተቋማዊ ሪፎርም በማካሄድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የንግድ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በሚያደርጉ እና የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚው መሪ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የክልሉ ነጋዴዎችና የቢዝነስ ባለድርሻ አካላት ከሀገር ውስጥ ባለፈ በውጭ ሀገራት ባሉ እድሎች የቢዝነስ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ልምድና ተሞክሮ እንዲቀስሙ ለማድረግ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተናግረዋል፡፡
አባል ምክር ቤቶች አቅማቸውን ማጎልበት እንዲሁም በምክር ቤቶች መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር ለማድረግ የልምድ ልውውጥ እና ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ የሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እንዲጠናከርም ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ሴት የቦርድ አባላትን ያካተተው የሶማሌ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተሻለ መልኩ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ እንደ አርዐያ የሚወሰድ መሆኑንም አቶ ሰብስብ ጠቁመዋል፡፡
የሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አህመድወሊ ሃሰን በበኩላቸው ምክር ቤታቸው በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረው በፋይናንስ እንዲሁም በቢሮ እና በሌሎችም አግባቦች ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ ከንግዱ ማኅበረሰብም ሆነ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡


እንደ ዋና መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከርም እንደ አባል ምክር ቤት ተቀራረቦ ለመስራት እንደሚፈልጉ ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን አቅም ለማሳደግ በምክር ቤቱ አደረጃጀት የአባላት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትን ከማጠናከር ባለፈ በቦርድ ኣባላት የሚመራ ልዩ የአባላት ጉዳይ ኮሚቴ በማቋቋም አቅማቸው እንዲያድግ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡
በውይይቱም የሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መሀመድ አብዲ እንዲሁም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ተገኝተዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia