Jul 05, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ዙሪያ ለቢዝነስ ተቋማት ተወካዮች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሥልጠና ሰጠ::




የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ዙሪያ ለቢዝነስ ተቋማት ተወካዮች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ነው።
ምክር ቤቱ ከGIZ አፍሪካ ህብረት የሥምምነቱ ድጋፍ ቡድን እንዲሁም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ የሥልጠና ፕሮግራም ከአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እሥከ ትላልቅ ኩባንያዎች ተወካዮች ተሣታፊ ናቸው።
ሥልጠናውም በዋናነት በኢትዮጵያ ታሪፍ ኦፈር፣ የኢንቨሥትመንት ፕሮቶኮልና በውድድር ፖሊሲ ፕሮቶኮል ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ምክር ቤቱ ከሚሠራቸው ተግባራት አንዱ የግሉ ዘርፍ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆንና ምርትና አገልግሎቶች የተሻለ ገበያ እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑን አንስተዋል።
ሥለሆነም በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ዙሪያ የተዘጋጀው ሥልጠናም በአፍሪካ ካለው ገበያ የሚገኘውን እድል በአግባቡ ለመጠቀምና ተወዳዳሪ ለመሆን ግንዛቤን ለማሣደግ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ሥልጠናውም የኢትዮጵያ ቢዝነሶች የተሻለ ዝግጁ እንዲሆኑ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማሥቻል የላቀ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።


