Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 12, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት እና የንግዱ ማኀበረሠብ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ።

 

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት እና የንግዱ ማኀበረሠብ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ።

ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም  “የንግዱ ማኀበረሠብ የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ የተካሄደው።

በአዲስ አበባ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር አብዱልሀኪም ሙሉ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር እንዲሁም የአዲስ አበባ፣ የኦሮሚያ እና የሸገር የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና ሠራተኞች እንዲሁም ከንግዱ ማኀበረሠብ የተውጣጡ አካላት በተገኙበት በእንጦጦ ፓርክ ተካሂዷል።

በተከላ ፕሮግራሙ ላይም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ደክተር አብዱልሀኪም ሙሉ መላው የንግዱ ማኀበረሠብ የአረንጓዴ አሻራ ሥራን እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሠረት በመውሠድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባው አሥገንዝበዋል።

ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና አካባቢ ጥበቃ፣ ለዘላቂ የአረንጓዴ ልማት መሣካት ትልቅ አሥተዋጽኦ ለሚያበረክተው የአረንጓዴ አሻራ መትከል ብቻ ሣይሆን መንከባከብም ዋነኛው ተግባር መሆን እንደሚገባው አሣሥበዋል።

 

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብሥብ አባፊራ አባጆቢር በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ ሥራን በባለቤትነት በመውሠድ ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ችግኝ ተከላ ለንግዱ ዘርፍ ትልቁ ትኩረት መሆኑን አንሥተዋል።

ምክር ቤቱ በተሻለ መልኩ እየተገበራቸው ካሉ የሪፎርም ሥራዎች አንዱ ማኀበራዊ ኃላፊነትን መወጣት መሆኑን  ያነሡት አቶ ሰብስብ የአረንጓዴ አሻራ ሥራም ትኩረት የተሠጠውና የንግዱ ማኀበረሠብም በየአካባቢው እየተገበረው ያለው ተግባር ነው ብለዋል።

“በመትከል ማንሠራራት” የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በእንጦጦ ፓርክ ሲካሄድ ከምክር ቤቶች የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በተጨማሪ የተለያዩ ድርጅቶች ሥራተኞች እና ባለሙያዎችም ተሣትፈዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia