Jul 21, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት የሱማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት የሱማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ገብተዋል።
የዳይሬክተሮች ቦርድ አመራሮች በቆይታቸዉ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር የንግድ ም/ቤቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ።
በም/ቤቱ ፕሬዘዳንት ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር የተመራዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑክ ጅግጅጋ አዉሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በሱማሌ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቦርድ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


