Aug 20, 2025 .
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተካሄደ ነዉ፡፡ ከከተሞቹም መካከል ጅማ፥ አሰላ፥ ሻሸመኔ እና ወሊሶ ከተሞች ይገኙበታል።

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተካሄደ ነዉ፡፡
ከከተሞቹም መካከል ጅማ፥ አሰላ፥ ሻሸመኔ እና ወሊሶ ከተሞች ይገኙበታል።
በጅማ ዞን ለግብርና ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶችን ለማምረት መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ኤግዚቢሽኑን በከፈቱበት ወቅት አስታውቀዋል።

በዞኑ የተመረቱ የግብርና ምርቶች ለሃገር ውስጥ ፍጆታ አልፈው ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑንም ተናግረዋል።
በኤግዚቢሽኑ ጅማ እና አካባቢዋ የሚመረቱ የግብርና ውጤቶች፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የባሕል አልባሳት እና በእጅ የተቀረፁ ቅርፃ ቅርፆች ለገበያ ቀርበዋል።
ኤግዚቢሽኑ በጅማ ዞን እና በከተማው ንግድ ፅሕፈት ቤት ቅንጅት የተዘጋጀ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል። (ምንጭ፥ ኦሮሚያ ንግድ ምክር ቤት እና ኢቢሲ)

