Aug 20, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከስራና ክህሎት ሚንስቴር ጋር በመተባበር በGIZ –STEP IV ፕሮጀክት የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ በማቋቋም ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከስራና ክህሎት ሚንስቴር ጋር በመተባበር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የግሉ ዘርፍ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ማፍራት ላይ አትኩረው እንዲሰሩ የሚያስተባብር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማስተባበርያ የስራ ክፍል (TVET Coordination Unit) በGIZ –STEP IV ፕሮጀክት የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ በማቋቋም ላይ ነው፡፡
የማስተባበርያ ስራ ክፍሉ ዋና ዓላማ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ኃይል እንዲያመርት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጎልበት ነው፡፡

የማስተባበርያ ክፍሉን ማቋቋም አስፈላጊነትና ትግበራውን በተመለከተ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሳፋየር አዲስ ሆቴል የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡
በአስፈላጊነቱና አተገባበሩም ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ፀደቀ ድጋፌ፣ በስራና ክህሎት ሚ/ር የሙያ ደረጃና ስርዐት ስልትና ዝግጅት እና ብቃትና ምዘና መሪ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ማርታ ወልዴ እንዲሁም በGIZ STEP IV ፕሮጀክት የግሉ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ሰብለወንጌል ሀረገወይን የመወያያ መነሻ ሀሳቦችን አቅርበዋል፤ ከባለድርሻ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡


