Sep 01, 2025 .
የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተባባሪነት በጥራት መንደር ተካሄደ።

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተባባሪነት በጥራት መንደር ተካሄደ።
ከዚሁ ጋራ ተያይዞም የሀገር ውስጥ ንግድ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፤ በውይይት መድረኩም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ ሲሆኑ ከውይይቱ አቅጣጫ አመላካችና መፍትሔ ጠቋሚ ሐሳቦች እንደሚነሱና ይህም አጠቃላይ የንግድ ስርዓቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልፀዋል ።

የፓናል ውይይቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ እየመሩት ሲሆን በፖናሊስትነትም የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሶፍያ ካሣ ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ( ተባባሪ ፕሮፌሰር ) እና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዉበታል።


