Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 11, 2025 .

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የንግዱ ማኅበረሰብ እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ:- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

           
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የንግዱ ማኅበረሰብ እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ዓመቱ የሰላምና የብልጽግና እንዲሁም የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በሀገራችን የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ሚና በሚፈለገው ደረጃ እንዲደርስ፤ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና የመላው ህዝባችን ኑሮ ተሻሽሎ የምንፈልገውን ልማትና ብልፅግና ማረጋገጥ እንዲቻለን በግሉ ዘርፍ አቅም ግንባታ፣ በምርምርና ፖሊሲ አድቮኬሲ እንዲሁም በስልጠና እና አረንጓዴ ልማት የሚጠበቅበትን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።

ካለፈው አመት ጀምሮም አጠቃላይ የተቋም ሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ በአዲስ አሰራርና አደረጃጀት የኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቶች እንዲተዋወቁ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆንና ምቹ የቢዝነስ ከባቢ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራን እንገኛለን፡፡

አዲሱ ዓመት መላው የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም አባል ምክር ቤቶች በትብብርና   አንድነት  መንፈስ በመስራት የበለጠ ውጤት የምናስመዘግብበት  የስኬትና የብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
አመሰግናለሁ!

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia