Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 18, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና  የአለም ባንክ የግሉ ዘርፍን  ተወዳዳሪነት ሊያጎለብቱ በሚችሉ የአቅም ግንባታ ተግባራት ዙሪያ በጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና  የአለም ባንክ የግሉ ዘርፍን  ተወዳዳሪነት ሊያጎለብቱ በሚችሉ የአቅም ግንባታ ተግባራት ዙሪያ በጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

የም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና  በአለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ልማት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ተሾመ የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ መጫወት የሚገባውን ሚና ለማጎልበት በሚያስችሉ የአቅም ግንባታዎች ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት   የአገሪቱ የግሉ ዘርፍ  በአህጉራዊና አለም-አቀፋዊ  ውድድር ውስጥ ብረቱ ተፎካካሪ ለመሆን ብቻ ሳይሆን ተፎካክሮም ተገቢውን የገበያ ድርሻ እንዲይዝ ከማድረግ አኳያ ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር እየሰራ መሆኑን ዋና ፀሐፊው ዶ/ር ቀነኒሳ አስረድተዋል፡፡

የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ በመደገፍ ከሚታወቀው የአለም ባንክ ጋርም በግሉ ዘርፍ አቅም ግንባታ ላይ ለመስራት ፍላጎት አንዳለው ገልፀዋል፡፡

በአለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ልማት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ተሾመ በበኩላቸው በተለይም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አሁን በተጀመረው የካፒታል ገበያ ወስጥ የሚፈጠረውን ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የሚያገኙትን ካፒታል በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል አቅም እንዲኖራቸው በስልጠና ማገዝና ለተወዳዳሪነት ብቁ ማድረግ ላይ የአለም ባንክ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው  ገልፀዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia