Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 19, 2025 .

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ  ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ  ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን በመፈረም እና በፓርላማ በማፀደቅ ከቀዳሚዎቹ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ግብይት እንዴት ይፈጸማል? አሰራሩስ በምን የህግ ማዕቀፎች ይመራል የሚሉ እና መሰል ጉዳዮችን የያዘ የትግበራ ስትራቴጂ መዘጋጀቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መግለፁን ሸገር ራድዮ ዘግቧል ።

የቀረጥ ሥርዓት የሚመራበት ሰነድም እንዲሁ በገንዘብ ሚኒስቴር መዘጋጀቱ ነው የተገለፀው።
ስምምነቱን ባጠረ ጊዜ ይፋዊ በሆነ ሥነ-ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ነግረውናል ሲል ነው ሸገር ኤፍ.ኤም ራድዮ  የዘገበው፡፡
ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት አቅማቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርም አዳዲስ አሰራሮች እንዲተዋወቁ እየሰራ እንደሚገኝ ነው በዘገባው የተገለፀው፡፡
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ሲወል በአህጉሩ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ወደ 33 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሁን ያለው የሀገራቱ የንግድ ልውውጥ ከ11 በመቶ እንደማይበልጥ ተነግሯል፡፡
Ethiopia has recently finalized its National AfCFTA implementation strategy
The Ministry of Trade and Regional Integration said that it will begin implementing the trade agreement in a very short time with an official ceremony. Ethiopia, which is one of the first countries to sign the African Free Trade Agreement (AfCFTA) and ratify it in parliament, has prepared an implementation strategy that includes issues such as how trade will be carried out? What legal frameworks will govern the process and similar issues.
The Ministry of Finance prepared the document that governing the tax System.
The Ministry of Trade and Regional Integration’s Communications Executive Officer, Mr. Wondimu Flatie, told Sheger FM that the agreement will begin implementing in a very short time with an official ceremony.
Ethiopian traders need to increase their capacity to be competitive once the agreement is implemented, and he told that the Ministry of trade and regional integration is also working to introduce new procedures.
The African Free Trade Agreement (AfCFTA) is expected to increase intra-African trade from the current 11 percent to 33 percent when fully operational.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia