Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 22, 2025 .

የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ ከEBS TV ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ያነሷቸዉ አንኳር ነጥቦች

የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ ከEBS TV ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ያነሷቸዉ አንኳር ነጥቦች
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራ ከEBS TV ጋር ቃለመጠይቅ አድርገዋል፡፡  ያነሱዋቸዉን አበይት ነጥቦች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተመሰረተ 80 ዓመት የሞላዉ መሆኑን እና በሀገራችን የንግድ  አገልግሎትን ለማሳለጥ የተቋቋመ አንጋፋ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ የማይሰራ የግሉ ዘርፍ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  1. የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አላማዎች እና ተግባራትን በተመለከተ
    •  ለንግዱ ማህበረሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት
    •  የአባላትን መብትና ጥቅም ማስከበር
    •  የአገሪቱ ምርቶችና አገልግሎቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም እንድታዋወቁ ማድረግ
    •  በአገሪቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲያድጉ (እንድስፋፉ) ማድረግ
    •  በመንግስትና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ማገልገል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
    2.  የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለንግዱ ማህበረሰብ ድምጽ ሆኖ የሚያገለግልና ጥብቅና የሚቆም ተቋም መሆኑን በተመለከተ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ያነሱት አበይት ነጥቦች
  • የንግድ ምክር ቤቱ ጥብቅና የሚቆመው አንድም በቀጥታ፤ሁለትም በተዘዋዋሪ የሚገለጽ መሆኑን፤
    •  ለምሳሌም የመንግስት ፖሊሲዎች አዋጆች ከመውጣታቸው በፊት በመንግስት ግብዣ የአዋጁ ረቂቅ ላይ እንድንወያይ የሚደረግ መሆኑን፤ ረቂቁ ላይ የራሳችንን (የም/ቤቱን) ሀሳብ የሚንሰጥ በአዋጁ ዉስጥም ሚዘናዊነቱን ጠብቆ እንዲካተት እንደሚደረግ
    •  አዋጁ ከወጣ በኋላም (በትግበራ ወቅት) አስኪያጅ ያልሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወይም  አዋጁ ችግር አለበት ተብሎ ከታሰበ በተቋሙ እንደሚጠና፤  የጥናት ውጤቱ ለመንግስት እንደሚቀርብ፤ በጥናቱ ላይ መንግስትና ባለድርሻ አካላት እንደዚሁም መንግስትና ባለጉዳዩ የንግዱ ማህበረሰብ ተገናኝቶ እንዲወያይ እንደሚደረግና የተሰጠዉን የመፍትሄ ሀሳብ ስራ ላይ እንዲዉል እንደሚደረግ
  1. ከግብር እና ከንግድ ስርዓት ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ የሚወጡ የአሠራር ማሻሻያዎችና አዳዲስ በሚወጡ ህጎች የንግድ ምክር ቤቱ ተሳትፎና ሚናን በተመለከተ
  • መንግስት ለግሉ ሴክተር የሰጠዉ ትኩረት መኖሩን፣ ከዛ አንጻር በሚወጡ አዋጆች ላይ የንግድ ም/ቤቱን በሰፊዉ የማሳተፍ ሁኔታዎች መኖሩን፣ ከዛም አልፎ ጫና የሚፈጥሩ አዋጆች የሚወጡበት ሁኔታ ሊኖር ቢችልም መንግስት የንግድ ም/ቤቱን ያላዳመጠበት ጊዜ አለመኖሩን
    •  ይህም በረቂቅ ህጎች ላይ ቀድሞ በመወያየት አዋጆችና ደምቦች ከተሻሻሉና ከወጡ በኋላም የግሉ ሴክተር ድምጽ ሆነን መንግስትን ከመሞገት ከመወትወትና የአድቮኬሲ ስራዎችን ከመስራታችን የተነሳ እንደዚሁም ከመንግስት ጋር በመነጋገርና በመደማመጥ ህጎች እንዲሻሻሉ የተደረገበት ሁኔታ የም/ቤቱ ድርሻ ሰፊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
  1. የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መጠናከርና አቅም መፍጠር ጤናማ የሆነ የተስተካከለ የቢዝነስ ስርዓት እንዲፈጠር ማስቻል ስለሆነ ከዚህ አኳያ ለንግዱ ማህበረሰብና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ስለ ሚኖራቸው አስተዋጽኦ በተመለከተ

•  በአለም ላይ የንግድ ምክር ቤት አስፈላጊነት አጠራጣሪ እንዳልሆነ፤ የንግድ ግንኙነት፣ የንግድ ዳኝነት ፣የንግድ ልውውጦች ከየትኛውም ሀገራት ጋር የሚደረገው በንግድ ምክር ቤት በኩል መሆኑን
•   ለምሳሌ ብዙ አገራት የምርት አገር ማረጋገጫ የሚሰጡት የንግድ ምክር ቤቶች መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡  የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትም አንዱ ከሚሰጠው አገልግሎት የምርት አገር ማረጋገጫ (Certeficate of Origin)  የሚሰጥ መሆኑን
•  የአድቮኬሲ ስራዎችን የሚሰራ መሆኑን
•  ንግድና ኢንቨስትመንት ወደ ሀገራችን እንዲሳብና እንዲስፋፋ የራሱን ሚና የሚጫወት መሆኑን
•  ያሉትን የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚያስጠናና የተጠኑትን የኢንቨስትመንት እድሎችን ለባለሀብቶች በማቅረብ ለእንቨስትመንት የሚጋብዝ መሆኑን
•  የንግዱ ማህበረሰብ ዉጭ ሄዶ በሰላም ገዝተው ሽጦ እንዲመለስ፤ እዚያ እንኳን ችግር ቢያጋጥመው እዚያ ካለው ንግድ ም/ቤት ጋር በመግባባት በመነጋገር እንዲፈታ የማድረግ ስራ በንግድ ምክር ቤታችን በኩል የሚሰራ መሆኑን

  1. ንግድ ም/ቤቱ ሀገራዊ ትርጉም ያለው ስራዎችን ለመስራት ራሱን እያበቃ ያለበትን አካሄድ በተመለከተ
  • ምክር ቤቶችን ጠንካራ ለማድረግ የመንግስት ፖሊሲ ወሳኝ መሆኑን
    •  አባላት ምክር ቤታቸውን ተቀብሎ ድርሻቸውንና ሚናቸውን መወጣታቸው አስፈላጊ  መሆኑን
    •  መንግስት ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ለአገር ግንባታ ማነቆ የሆኑትን ባአጠቃላይ ፖሊሲዎችን ቢቀይርም አሁን ያለዉ የንግድ ም/ቤቱ አዋጅ ለብዙ አመታት የቆየና ኢትዮጵያ የያዘችዉን የልማት እቅድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማስፈጸም እንደማይመጥንና አዋጁን ለማሻሻል ረቂቁ ለመንግስት ተልኮ እየተጠበቀ መሆኑን
    •  በመሆኑም ለጥንካሬ ማጣቱ መድረስ ያለበት ቦታ ያመድረሱ፣ ሚናዉን በአግባቡ አለመወጣቱ ወቅቱን የዋጀ የሚያሰራ አዋጅ አለመኖሩ ምክኒያት መሆኑን
    •  ይሁን እንጂ ንግድ ም/ቤቱ አዋጁ ባለመሻሻሉ እጁን አጣጥፎ ያልተቀመጠና ም/ቤቱን አዲስ መዋቅር በመዘርጋት፣ በአዳዲስ የሰዉ ሃይል በመገንባት፣ የገቢ ምንጩን በማሻሻል፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመዘርጋት፣ አባል ለሆኑም ሆነ አባል ላልሆኑ ሁሉ ሳያዳላ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ም/ቤቱ አላማዉን እያሳካ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
    6.  የንግድ ም/ቤቱ አባላት፣ የአባልነት መስፈርት እና የአባልነት ትሩፋትን በተመለከተ
  • የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 13 የክልል ምክር ቤቶች፣ 6 የዘርፍ ማህበራት፣ 2 የከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ ባጠቃላይ 21 የንግድ ምክር ቤቶች በአባልነት እንዳለዉ
    •  በእነዚህ 21 ምክር ቤቶች ስር ደግሞ የተለያዩ በየከተማው የተደራጁ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ተደራጅተዉ እየሰሩ መሆኑን
    •  የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና በስሩ የሚገኙት አባላት እና መዋቅራቸዉ ለሁሉም የንግዱ ማህበረሰብ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን  ጨምሮ ሳያዳሉ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡:
    7.  ተቋሙ የተሻለ ግንዛቤና አረዳድ እንዲፈጠር መሰራት ያለበትን በተመለከተ
    •  በቂ ግንዛቤ በመፍጠሩ ዙሪያ በስፋት መሰራት ቢኖርበትም፤ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትም ሆነ ታች ያሉት ቅርንጫፍ ንግድ ምክር ቤቶቻችን የግሉ ሴክተር ጥላና ከለላ እንዲሁም አንደበታቸዉ መሆናቸዉን መረዳት እንደሚገባ
  • የንግዱ ማህበረሰብ የድጋፍ ደብዳቤዎችን፣ የግልግል ዳኝነትን፣ስልጠናዎችን የፈለገ ቀን ብቻ ወደ ም/ቤቱ መምጣት እንደሌለበት
    •   የንግዱ ማህበረሰብ ተቋሙ የኔ ተቋም ነዉ ብሎ አባል በመሆን በቅርብ አብሮ መስራት  እንዳለበት አበይት መልእክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ (መሀመድ ቃሲም)

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia