Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 02, 2025 .

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ  የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አመራሮች በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መሠረታዊ መርሆች ላይ በሆሳዕና ከተማ ስልጠና ተሰጠ።

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ  የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አመራሮች በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መሠረታዊ መርሆች ላይ የግንዛቤ መፍጠርያ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ  እየተሰጠ ነዉ።

ስልጠናዉ የተዘጋጀዉ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት መክር ቤትና በGIZ Programme Support to Afrca ትብብር ሲሆን ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) የአገራችን የግሉ ዘርፍ እየገባበት ላለዉ አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ብርቱ ፉክክሮች ከወዲሁ እራሱን ማዘጋጀት አለበት ብለዋል።

የአገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ የግሉ ዘርፍ መጠናከር አለበት ያሉት ዋና ፀሐፊዉ ለግሉ ዘርፍ መጠናከር ደግሞ በየደረጃዉ ያሉት የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቶች መጠናከር እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሳኒ ሀሰን በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አመራሮች በወቅታዊዉና ወሳኙ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙርያ ተገቢዉን ግንዛቤ አግኝተዉ በዚህ ልክ አባሎቻቸዉን የማስገንዘብና የማዘጋጀት ስራ እንዲሰሩ ስልጠናዉን በማመቻቸቱ አመስግነዋል።

የግንዛቤ መፍጠርያ ስልጠናዉን የሰጡት በGIZ AU የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑ  አቶ ዉብእሸት ካሳ ሲሆኑ  የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መሠረተ ሀሳቦች: ዋና ዋና ምሶሶዎች: ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸዉ በስልጠናዉ ተዳሰዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮችና በየደረጃዉ ካሉ የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች የተዉጣጡ አመራሮች በስልጠናዉ እየተሳተፉ ነዉ።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia